Skip to main content

ከቋራ እስከ አርማጭሆ ወልቃይት ጠገዴ ሁመራ ሰሊጥ አጨዳ ለመሄድ አማራጭ መንገዶች

 


ከቋራ እስከ አርማጭሆ ወልቃይት ጠገዴ ሁመራ 


• ከተለያዩ ክፍለ-ሀገሮች በመነሳት ወደ ሰሊጥ አጨዳ ለመሄድ አማራጭ መንገዶች!!!!

•  ከጎንደር ~ሳንጃ ~ ሶሮቃ ~እርጎዬ ~በመጓዝ አብርሃጅራ ላይ በመውረድ ወደ አብደራፊና ኮርሁመር ወደ ማርዘነብና ስናር እንዲሁም ወደ ቀጭኔና ጎደቤ የኢንቨስትመንት ቀጠና መድረስ ይቻላል

•  ከጎንደር ~ሳንጃ ~አሸሬ ላይ በመዉረድ ወደ ደለሳና ወደ ጋብላ የእርሻ ኢንቨስትመንት ቦታዎች መግባት ይቻላል፡፡

• ከጎንደር ዳንሻ በመዉረድ ~ማይደሊ ድቭዥን እና  እብናትን ጨምሮ የዳንሻን ከጎንደር ~ሁመራ በመዉረድ ወፍ አርግፍ የቃብትያ~ አካባቢን  ማግኘት ይቻላል።

• ከጎንደር በዕከር በመዉረድ የባህረ ሰላምን ጭምሮ አካባቢውን ማግኘት ይቻላል።
•  ከጎንደር ሁመራ በመዉረድ  የማይካድራ እና በረከት አካባቢን ማግኘት ይቻላል።
•  ከጎንደር ሳንጃ ሰጋሎ ቅራቅር በመዉረድ የአዴት የጠገዴን አካባቢን ማግኘት ይቻላል።
• ሳንጃ ~ሶሮቃ~እርጎዬ ~ኪሻ ላይ በመዉረድ ወደ ጠገዴ የእርሻ ቦታዎችና ወደ መሃርሽ እንዲሁም ወደ ዘመነ መሪቅ እና ድርማጋ መግባት ይቻላል።
• ከጎንደር አዘዞ~ቆላድባ ደልጊ ~ሻውራ ~በሙር ላይ በመውረድ ወደ አባይዳር የኢንቨስትመንት ቀጠና መግባት ይቻላል።
ከ ጎንደር አዘዞ ~ ቆላድባ~ ደልጊ~ ሻውራ~ በሙር ገለጉ~ ዱባባ ላይ በመውረድ ወደ ምርት ገለጉ እና ነብሰ ገበያ የ ኢንቨስትመንት ቀጠናወች መግባት ይቻላል።
ከ ጎንደር አዘዞ ቆላድባ~ ደልጊ ሻውራ ~በሙር ገለጉ~ ዱባባ ~ሽንፍ ላይ በመውረድ ወደ ነብሰ ገበያ እና ቁጥር 4 የ ኢንቨስትመንት ቀጠናወች መግባት ይቻላል።
ከ ጎንደር~ ቆላድባ ~ደልጊ ~ሻውራ ~በሙር  ገለጉ~ ዱባባ~ ሽንፍ በኩል ወደ ~ገንድ ውሃ መስመር
• በጎጃም በኩል ደግሞ
• ከባህርዳር - ጭምባ - ቁንዝላ - ሻሁራ - ገለጎ - ወደ ቋራ - መተማና ሌሎች መግባት ይቻላል።
ከዱርቤቴ - ይስማላ - ሊበን - ቁንዝላ - ሻሁራ - ገለጎ - (ወደ ቋራ -መተማና ሌሎች) መግባት ይቻላል።
• በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው ከቋራ እስከ ሁመራ ያለው ምድር እጅግ ውብ፣ ለአይን የሚያሳሳ፣ ሰፋፊ የእርሻ ቦታ ያለው
• የነጭ ወርቆች ምድር (ሰሊጥ ፤ አኩሪ አተር ፤ ሱፍ ፤ ጥጥ፤ ማሽላ ፤ ሩዝ ፤ ማሾ የሚመረቱበት)
• አመቱን ሙሉ የሚፈሱ ትልልቅ ወንዞች ያሉበት በመሆኑ በቂ የውሃ ሀብት ያለው
• አስተማማኝ የዝናብ መጠን ያለው 
• ምቹ ስነ-ምህዳር (ለሰብል ፤ ለእንስሳት ፤ ለመስኖ ፤ ለደን ልማት እጅግ የተመቼ)
•  ለጥ ያለ፣ ዳርቻው ከሰማይ ጋር የተያያዘ የሚመስል
• ለም መሬት ያለው ድንቅ ምድር  ነው፡፡
• ምዕራብ ጎንደር ብቻ ከ516ሺህ ሄክታር በላይ መሬት
• ለሰብል ልማት ምቹ ሲሆን በ2014/15 የምርት ዘመን ከ493ሺህ ሄ/ር በላይ መሬት በልዩ ልዩ ሰብሎች የተሸፈነ መሆኑን ከዞኑ ግብርና መምሪያ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
• አኩሪ አተር ብቻ ከ127ሺህ ሄ/ር በላይ መሬት ተዘርቷል፡፡ ካለው ጠቅላላ መሬት ውስጥ ከ300ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ መልማት የሚችል ነው፡፡
• ከቋራ እስከ ሁመራ ያለው ድንቅ ምድር በአግባቡ በዘመናዊ ግብርና ስርዓት ቢለማ ሀገርን በእጅጉ መቀየር የሚችል፣ በሀገሪቱ ግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ ታዕምር መፍጠር የሚችል አጓጊ ቀጠና ነው፡፡
• አካባቢው ከጎረቤት ሀገር ሱዳን ጋር በምዕራብ አቅጣጫ ሙሉ ለሙሉ የሚዋሰን በመሆኑ በተደጋጋሚ ለጸጥታ ስጋት ተጋላጭ ቢሆንም በጭንቅ ጊዜ ተኳሽ በሰላም ጊዜ አራሽ፣ በአንድ እጁ ትራክተር በሌላ እጁ ጠመንጃውን ይዞ የልማት ስራውን የሚያሳልጥ ጀግና ማህበረሰብ ያለበት አስገራሚ ምድር ነው!!

Comments

Popular posts from this blog

አርሲ እና የአርሲ ሴቶች ባህል

  በዳዊት ፀሐይ አርሲ በማዕከላዊ የኢትዮጵያ ክፍል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኝ ክልል ነው።  በዋናነት በአካባቢው በሚኖሩ በአርሲ ሰዎች ስም ተሰይሟል።  የአርሲ ዞን ወደ 17,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ከ3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይኖራል።  ክልሉ በተለያዩ መልክዓ ምድሮች የሚታወቅ ሲሆን ይህም ደጋ፣ ቆላማ እና ደኖችን ያጠቃልላል።  በተጨማሪም የላንጋኖ ሀይቅ እና የዝዋይ ሀይቅን ጨምሮ የበርካታ ወንዞች እና ሀይቆች መኖሪያ ነው።  በአርሲ ያሉ አብዛኛው ሕዝብ ዋናው የገቢ ምንጭ ግብርና ነው።  ክልሉ ቡና፣ ሻይ፣ በቆሎ፣ ስንዴ እና ሌሎች ሰብሎችን በማምረት ይታወቃል።  የእንስሳት እርባታ የኢኮኖሚው አስፈላጊው አካል ነው። አርሲ ካሏት ባህላዊ ቅርሶቿ በተጨማሪ የበርካታ ታሪካዊ ቦታዎች ባለቤትም ናት።  ከእነዚህም መካከል በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጀመረው አዳዲ ማርያም ውቅር ቤተ ክርስቲያን እና የሶፍ ኦማር ዋሻ ( ከአፍሪካ ትልቁ የዋሻ ስርዓት አንዱ ነው። ) ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው፠ በአጠቃላይ አርሲ ልዩ የሆነ ባህልና ታሪክ ያላት በመልክአ ምድርና በተፈጥሮ ሀብት በእጅጉ የበለጸገች  ክልል ናት። በአርሲ ባህል ሴቶች ትልቅ ሚና አላቸው።  ቤተሰብን የማስተዳደር፣ ልጆችን የማሳደግ እና በቤተሰቡ ገቢ ላይ በእርሻ ወይም በትንንሽ ንግዶች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው።  ሴቶች በማህበረሰብ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች በተለይም ከማህበራዊ ደህንነት እና ልማት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ። በአለባበስ ረገድ የአርሲ ሴቶች በተለምዶ ሸማ የሚባል የባህል ልብስ ይለብሳሉ። ከጥጥ የተሰራ እና በቀለማት ያሸበረቀ ነው።...

ነጻ የወጣችውን ራያ ቆቦን ወገን ለመቼ ነው በሚል ስፍራው ጋ ደርሰን የህዝቡን አኗኗር እና ስነ ልቦና አይተናል።

   ከብዙ በጥቂቱ ፥ ከሙሉ በክፍሉ ነጻ የወጣችውን ራያ ቆቦን ወገን ለመቼ ነው በሚል ስፍራው ጋ ደርሰን የህዝቡን አኗኗር እና ስነ ልቦና አይተናል።ከሁለት ዓመት በውኋላ ተቋርጦ የነበረው መብራት ስለ መጣ ከተማው በተኩስ ሲናጥ አድሯል።   ቆቦ በሰሜን ኢትዮጵያ ÷ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የምትገኝ ከተማ ናት  ቆቦ ከባህር ጠለል በላይ 1468 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች።   ቆቦ በምዕራብ በኩል በኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች እና በምስራቅ በአፋር የእሳተ ጎሞራ ጭንቀት ያዋስናታል።  በታሪክ ራያ አንጎት ተብላ ትጠራ ነበር። ራያ ቆቦ የአማራ ህዝብ ነው። አንጎት በአማራ ክልል ወልድያ አቅራቢያ ከሀብሩ ወረዳ በደቡብ በኩል እስከ ማይጨው ራያ አዘቦ የሚደርስ ሜዳ ነው።  ይህ ስፍራ ከኢፋት ሱልጣኔት (13ኛው ክፍለ ዘመን) ጊዜ ጀምሮ በክርስቲያን ደጋማውያን እና በምስራቅ በመጡ ሙስሊሞች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ውስጥ ነበር።  አብዛኛው ቀደምት ግጭት የተካሄደው በደቡብ በኩል በምስራቅ ድንበር ነበር። አሁን ሸዋ ነው።   ነገር ግን በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንጎት አሁን ራያ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በአዳል ጀነራል አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ጋዚ ጦር እና በኢትዮጵያው አጼ ልብነ ድንግል ከፍተኛ ግጭት ጊዜ የውጊያ መዐከል ነበር። ይህ አስነዋሪ የግጭት ዘመን የኢትዮጵያና የአዳል ጦርነት በመባል ይታወቅ ነበር።  አጼ ልብነ ድንግል የካቲት 10 ቀን 1541 ምጽዋ ወደብ ከደረሱት ፖርቹጋሎች እርዳታ ጠየቁ። በሚያዚያ ወር 1542 የሁለቱ ሠራዊት ከአሸንጌ  ሃይቅ በስተሰሜን በኮረም አካባቢ ተገናኙ። ይህም ውጊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ ጦር መ...

የወላይታ ንጉስ ካኦ ጦና

በዳዊት ፀሐይ  ካኦ ጦና በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ የገዛ የወላይታ ንጉስ ነበር።  ወላይታ በደቡብ ኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የሚገኝ ክልል ነው።  የራሱ የሆነ ቋንቋ እና ባህል ያለው የወላይታ ህዝብ መኖሪያ ነው።  ክልሉ በቡና ምርት የሚታወቅ ሲሆን በተፈጥሮ ውበቱ የቱሪስት መዳረሻም ነው።  እናም ካኦ ጦና በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን የኢትዮጵያን ግዛት መስፋፋት በመቃወም ይታወቃሉ።  ካኦ ቶና ህዝቡን እየመራ ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ተከታታይ ጦርነት ቢያደርግም በመጨረሻ ግን ተሸንፎ እጅ ለመስጠት ተገደደ።  በስደት ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ኖረ።  ካኦ ቶና ቢሸነፍም በወላይታ ህዝብ ዘንድ እንደ ጀግና ሲታወስ ቆይቷል።  ትሩፋቱ በወላይታ አፈ ታሪክ እና ዘፈኖች የተከበረ ሲሆን ታሪኩ አሁንም ጭቆናን እና ኢፍትሃዊነትን ለመቃወም ይውላል። ስለ ጦርነቱ ማለትም ስለ ካኦ ጦና እና ዳግማዊ አጼ ምኒልክ መካከል ስለተደረጉ ጦርነቶች ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይቻላል።  ሆኖም ካኦ ጦና ህዝባቸውን በመምራት በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ተከታታይ የሽምቅ አይነት ጥቃቶችን ማለትም እንደ ማሸማቀቅ እና መምታት የመሳሰሉ ስልቶችን ሲጠቀሙ እንደነበር ታሪክ ያወሳል። ዳግማዊ አፄ ምኒልክም አመፁን ለመደምሰስ ብዙ ጦር ልከው ነበር።  ጦርነቱ ለብዙ አመታት የዘለቀ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባቸዋል።  በመጨረሻም ካኦ ጦና ተሸንፎ እጅ ለመስጠት ተገዷል።  በስደት ወደ አዲስ አበባ ተወስዶም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ኖሯል። ፊታውራሪ ደስታ ፍስሐ የካኦ ጦና ልጅ