"እንኳን ለራሳችን ለሌሎች የሚተርፍ ስንዴ ማልማት እንችላለን፤ ለዚህም መንገዱን ጀምረነዋል።" - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በሱማሌ ክልል ፋፈን ዞን ቱሉጉሌት ወረዳ ኩሉሌ ቀበሌ በመገኘት ሀገራዊ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ "እንኳን ለራሳችን ለሌሎች የሚተርፍ ስንዴ ማልማት እንችላለን፤ ለዚህም መንገዱን ጀምረነዋል። ለዚህ ትልቁ ማሳያ ሱማሌ ክልል ነው። በሄክታር 40 ኩንታል ማምረት የሚቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል" ብለዋል።
ዘንድሮ በበጋ ስንዴ አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 52 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማግኘት ዕቅድ ተይዟል።
ይህም የአገሪቷ ፍጆታ ሙሉ ለሙሉ ከማሟላት ባለፈ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚያስችል ተገልጿል።
ዘንድሮ ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ ለውጭ ገበያ እናቀርባለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ባለፈው ዓመትም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 24 ነጥብ አምስት ሚሊዮን ክንታል ስንዴ መገኘቱን ግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
ባለፋት አራት ተከታታይ ዓመታት በበጋ ስንዴ ልማት ለተገኘው አመርቂ ውጤትም የጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነት፣ የተቀናጀ የፋይናንስ ድጋፍና አገራዊ የስንዴ የመስኖ ፕሮጀክት አስተባባሪ ጽህፈት ቤት መዘርጋቱ ከፍተኛ ሚና ማበርከቱን ተገልጿል ።

Comments
Post a Comment