የማሳይ ጎሳ መንግስትን ከርስቴ ሊነቅለኝ ነው ብሎ የይገባኛል ጥያቄ አቅርቧል። ለፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት አቅዷል። የፍርድ ቤቱ ክስ እ.ኤ.አ. ከ2017 ጀምሮ ማሳይን ከ1,500 ካሬ ኪ.ሜ. የሴሬንጌቲ ብሔራዊ ፓርክ አዋሳኝ መሬት ማፈናቀልን ያካትታል። ፍርድ ቤቱ እ.ኤ.አ. በ 2018 የማሳይ ጎሳ ከቤት ማስወጣት ጊዜያዊ ትዕዛዝ አውጥቷል።
ነገር ግን በፍርድ ክርክራቸው ማሳኢዎች ከሴሬንግቲ ፓርክ እንጂ ከመንደር መሬታቸው እንደተባረሩ ማሳየት አልቻሉም እና ተወስኖባቸዋል። በኃይል ተፈናቅለናል ያሉት ምስክሮችን የአካል ጉዳትና ኪሳራ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሳይሰጡ መቅረታቸውንም ፍርድ ቤቱ ገልጿል።
የአመልካች ጠበቃ አስቴር ሙናሮ፣ “በምስራቅ አፍሪካ የፍትህ ፍርድ ቤት ይግባኝ የመጠየቅ መብት አለን "ይህ ቀጣዩ እርምጃችን እንደሚሆን እና ዛሬ ካገኘነው የተለየ ፍርድ እንደሚሰጠን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።
በቱሪዝም ላይ የተመሰረተው የታንዛኒያ መንግስት በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።

Comments
Post a Comment