ሉሲ ወደ ትግራይ ኢትዮጵያ ዘልቀን አቡነ የማዕታ ጉህን እናስታውስ ትላለች።
አቡነ የማዕታ ጉህ በዓለም ላይ ካሉት እጅግ አስደናቂ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ነው።
ገደሉ ከ650 ጫማ በላይ ነው።
በሚያማምሩ ተራሮች እና ሸለቆዎች የተከበበ ነው።
ገዳሙ በጣም ዝነኛ ነው።
በ 500 ዓመተ ምህረት አካባቢ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በአቡነ የማዕታ ጉህ የተመሠረተ ነው።
በመኪናም ሆነ በታክሲ ሥፍራው ጋር ለመድረስ ምቹ ነው።
አቡነ የማዕታ ከ650 ጫማ በላይ ገደል የሆነውን ተራራ ለገዳምነት የመረጡት
4ኛዋን ሰማይ መንግሰተ ሰማያትን ስለ ሚናፍቁ ነው።
ቤተክርስቲያኑ ለብዙ መቶ ዘመናት ለምዕመኑ ማስቀደሻ ፥ መጠመቂያ ፥ መቆረቢያ እና መቀበሪያ ሆኖ የኖረ ነው።
ቤተ ክርስቲያኑ ወደ 20 የሚደርሱ አገልጋዮች አሉት።
ከ47 ዓመታት በላይ የኖሩት አባት ገዳሙን ያስተዳድራሉ።
በየቀኑ 650 ጫማ በላይ የሆነውን ገደል መውጣት እና መውረድ አስመርሯቸው አያውቁም።
ውስጥ በቅዱሷት ስዓላት የማረ እና የተዋበ ነው።
በተቀደሰው ሥፍራ በአበነ የማዕታ ጉህ ደብር ስተርፍ የሚሰማህ ስሜት በሰማይ እንዳለህ ነው።
Comments
Post a Comment