ሄልምከን ፏፏቴ ጽንፍ ነው። ጽንፍ እየጨመረ የሚሄድ አጽናፍ ቦታ ነው።
ሄልምከን ዱር ነው።
ሄልምከን ቆንጆ ነው።
ሄልምከን አስቸጋሪ እና ኃይለኛ ቦታ ነው።
እርስዎን በደቂቃ ውስጥ ከመኖር ወደ አለመኖር ሊለውጥ የሚችል ትልቅ ፏፏቴዎች አሉት።
ሄልምከን ፏፏቴ በጣም ከባድ ነው።
በእንደዚህ ዓይነት አስቸጋሪ ተራራ ላይ መውጣት በአንድ እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፑል አፕዎችን ከማድረግ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ወይም ደግሞ በከፍተኛ ኮሪዮግራፍ የተሰራ የባሌ ዳንስ እንደ መስራት ነው።
ማንም ሰው ከዚህ በፊት ሞክሮት ወይም ወጥቶት አያውቅም።
ዋና ኃሳቡ ከፏፏቴው ስር እስከ ፏፏቴው ጫፍ ድረስ ያለውን መስመር ለመስራት ነው።
ሄልምከን ፏፏቴ በብሪቲሽ ኮሎምቢያ ውስጥ ያለ ፏፏቴ ነው።
ሄልምከን ለመጀመሪያ ጊዜ በዋይን ሂዩዝ፣ ዴቪድ ዲናርድ እና ኤሪክሰን ዴቪስ በ1972 የተገኘ አስቸጋሪ እና አስፈሪ ደግሞም ማራኪ ስፍራ ነው።
ተራራ የሚወጡት በሄልምከን ተራራ የምናደርገው ጉዞ በህይወት ዘመን ውስጥ ታትሞ የሚቀር አንድ ትውስታ ነው። የምንችለውን ያህል እናድርጋለን። ይላሉ።
ግን በጣም አደገኛ ሊሆን እንደሚችልም ያውቃሉ። አደጋዎቹ የማይቆጠሩ ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። የሕይወትም ፍጻሜ ሊሆን ይችላል።
Comments
Post a Comment