Skip to main content

የጁ-ወልዲያ ያበቀለው ጀግናው አርበኛ የወሎው ፋኖ ሞገስ ከበደ በግርምት አፍ ያስያዘ ጀብድ ፈጽሟል።

 


ይሄ የጁ-ወልዲያ ያበቀለው ጀግናው አርበኛ የወሎው ፋኖ ሞገስ ከበደ ነው!

--------
የጀግና ተግባሩ እንጂ አፉ አይናገርም። ሞገስ ከበደ የወልዲያ ከተማ፣ ጊራና፣ የራያ  እና መሃል አምባ ልጆችን ይዞ በትናንትናው የጎብየ ግንባር ትግል በታሪክ ከፍ ብሎ የሚነገር፣ ልብን የሚያሞቅ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮችን በግርምት አፍ ያስያዘ ጀብድ ፈጽሟል።

"ሞገስ ከዚህ በላይ ማለፍ በቀጣይ ጦርነት እንዳንሳተፍ የሚያደርግ አደጋ ላይ ይጥለናል" ብየ እጁን ያዝኩት ይላል ጠባቂው አህመድ መሐመድ!
ቀኝ እጄን ቀምቶ፣ ተተኳሽ የጨረሰ ክላሹን አዝሎ፣  "ይልቁን ራቅ ብለህ መሬት ያዝና እራስህን እየጠበቅክ  ሽፋን ስጠኝ" ብሎ ከጎኑ የታጠቀውን ፈንጅ ነቅሎ ወደ እሳቱ መሃል ገባ። የታዘዝኩትን አደረግኩ ይላል ጓዱና ጠባቂው።  ቀኑ ለጠላት የሞትና ውርደት ነበር፥ ሞገስ ከበደ እና ልጆቹ ለጠላት የማይቀመሱ ሆነው ዋሉ።

የወልዲያ፣ ጊራና እና መሃል አንባዎቹ ወጣቶች ገድል ለታሪክ ይቀመጥ። በዚህ ፍልሚያ ከማንም በላይ በራያ ግንባር ላይ ተቆጥተው የዋሉ፣ ለራያ ህዝብ ነፃነትና የልብ ኩራት የተዋደቁ እነሱ ነበሩ። ነብሱን በጨርቅ ቋጥሮ አሻግሮ ለሚመለከታቸው አስመሳይ የወንዜ ልጅ ሁሉ ትምህርት አስተላልፈዋል። ብቸኛው ምርጫችን አንድ መሆን፣  ለአንድ አላማ መታገልና መሞት ድልን እንደሚያቀዳጅ አሳይተዋል። ህወኃትን የመሰለ ጉንዳን ሃይል በመለያየትና በማስመሰል ማሸነፍ እምደማይቻልም አሳይተዋል።
እነዚህ ጀግኖች ሌላው ቀርቶ እጃቸው ውስጥ የገቡትን ምርኮኞች በብስጭትና እልክ ከማንገላታት ተቆጥበው ፥
"እንዲህ እንዲያልቁ ምክንያት የሆናቸውን እብደት ጠይቋቸው" ብለው ለአለቃቸው  አስረክበዋል፥ ልዕለ ስብዕናና ጀግንነት ማለት እንደዛ ነው።

የራያ ወርቄው ቡቃያ መሐመድ ሰኢድ ሱሩር የአለቃውን ሞገስ ከበደን ቁጣ፣ ልመናና ተግሳጽ በእልክና ጀብድ ተላልፎ በክብር ወድቋል። "እነዚህ የራያ ታዳጊ የወርቄ ወጣቶች ተኩስ ውስጥ ሲገቡ ሰውነታቸው ይሞቃል፣ ባሩድን እንደ ጅራፍ ግርፊያ ቡታ የመቁጠር ጀብድ አለባቸው" ይላል አለቃቸው። 
የመሀል አንባው ጀግና ደምሌ ፈንታው፣ የመርሳው ነብር ሞላ ከበደ እና የእዜቱ ታደሰ ጋሻዉ  24 ሰዓት ተዋግተዋል። ሁለቱ ጀግኖች በትግል ላይ የተሰው ሲሆን ደምሌ ፈንታው ግዳጁን በተሳካ ሁኔታ አሳክቶ ሲመለስ ከርቀት በተተኮሰ የጠላት ኢላማ በክብር ወድቋል። የሌሎቹን አናብስት ግዳይ ሳይጨምር ደምሌና ጓደኛው በአንድ ዙር ብቻ  ከአስር በላይ ከባድ የሆኑ የጠላት ሃይል ተኳሾችን አሰናብተዋል። ክብር ለመሃል አምባው አርበኛ ፋኖ ደምሌ እና ጓዶቹ ይሁን!!
-------
ወራሪው ሃይል ሶስት ዙር በገባበት በዚህ ግንባር አንድም ጊዜ ሙት ሳያነሳ ለመሸሽ ተገዷል። የሚደንቀው ነገር ጠላት ትጥቁን ቀርቶ ያስቀመጠውን መገናኛ ሬድዮ ለማንሳት ፋታ ሳያገኝ ሲገረፍና ሲረግፍ ውሏል።

"ተልዕኮህን በተሳካ ሁኔታ ተወጥተሃል፣ ቦታውን ለቀህ ውጣ ወይም ተጨማሪ ቦታ ልስጠህ? ሲል  አዛዥ ክረኔሉ ሞገስ ከበደን ጠየቀው።
"ጠላት ይሄንን ቦታ ለቆ ሳይወጣ  አልወጣም፣ ቦታ ስጠኝ"  አለ ጀግናው! ባደረበት ግንባር እንደገና ዋለበት። ከሀምሳ በላይ የነብስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዎችን ማርኮ በክብርና ሞገስ ምሽጉን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስረክቦ ወታደሮቹን አስከትሎ እየተንጎባለለ ወጣ። 

Comments

Popular posts from this blog

አርሲ እና የአርሲ ሴቶች ባህል

  በዳዊት ፀሐይ አርሲ በማዕከላዊ የኢትዮጵያ ክፍል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኝ ክልል ነው።  በዋናነት በአካባቢው በሚኖሩ በአርሲ ሰዎች ስም ተሰይሟል።  የአርሲ ዞን ወደ 17,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ከ3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይኖራል።  ክልሉ በተለያዩ መልክዓ ምድሮች የሚታወቅ ሲሆን ይህም ደጋ፣ ቆላማ እና ደኖችን ያጠቃልላል።  በተጨማሪም የላንጋኖ ሀይቅ እና የዝዋይ ሀይቅን ጨምሮ የበርካታ ወንዞች እና ሀይቆች መኖሪያ ነው።  በአርሲ ያሉ አብዛኛው ሕዝብ ዋናው የገቢ ምንጭ ግብርና ነው።  ክልሉ ቡና፣ ሻይ፣ በቆሎ፣ ስንዴ እና ሌሎች ሰብሎችን በማምረት ይታወቃል።  የእንስሳት እርባታ የኢኮኖሚው አስፈላጊው አካል ነው። አርሲ ካሏት ባህላዊ ቅርሶቿ በተጨማሪ የበርካታ ታሪካዊ ቦታዎች ባለቤትም ናት።  ከእነዚህም መካከል በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጀመረው አዳዲ ማርያም ውቅር ቤተ ክርስቲያን እና የሶፍ ኦማር ዋሻ ( ከአፍሪካ ትልቁ የዋሻ ስርዓት አንዱ ነው። ) ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው፠ በአጠቃላይ አርሲ ልዩ የሆነ ባህልና ታሪክ ያላት በመልክአ ምድርና በተፈጥሮ ሀብት በእጅጉ የበለጸገች  ክልል ናት። በአርሲ ባህል ሴቶች ትልቅ ሚና አላቸው።  ቤተሰብን የማስተዳደር፣ ልጆችን የማሳደግ እና በቤተሰቡ ገቢ ላይ በእርሻ ወይም በትንንሽ ንግዶች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው።  ሴቶች በማህበረሰብ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች በተለይም ከማህበራዊ ደህንነት እና ልማት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ። በአለባበስ ረገድ የአርሲ ሴቶች በተለምዶ ሸማ የሚባል የባህል ልብስ ይለብሳሉ። ከጥጥ የተሰራ እና በቀለማት ያሸበረቀ ነው።...

ነጻ የወጣችውን ራያ ቆቦን ወገን ለመቼ ነው በሚል ስፍራው ጋ ደርሰን የህዝቡን አኗኗር እና ስነ ልቦና አይተናል።

   ከብዙ በጥቂቱ ፥ ከሙሉ በክፍሉ ነጻ የወጣችውን ራያ ቆቦን ወገን ለመቼ ነው በሚል ስፍራው ጋ ደርሰን የህዝቡን አኗኗር እና ስነ ልቦና አይተናል።ከሁለት ዓመት በውኋላ ተቋርጦ የነበረው መብራት ስለ መጣ ከተማው በተኩስ ሲናጥ አድሯል።   ቆቦ በሰሜን ኢትዮጵያ ÷ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የምትገኝ ከተማ ናት  ቆቦ ከባህር ጠለል በላይ 1468 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች።   ቆቦ በምዕራብ በኩል በኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች እና በምስራቅ በአፋር የእሳተ ጎሞራ ጭንቀት ያዋስናታል።  በታሪክ ራያ አንጎት ተብላ ትጠራ ነበር። ራያ ቆቦ የአማራ ህዝብ ነው። አንጎት በአማራ ክልል ወልድያ አቅራቢያ ከሀብሩ ወረዳ በደቡብ በኩል እስከ ማይጨው ራያ አዘቦ የሚደርስ ሜዳ ነው።  ይህ ስፍራ ከኢፋት ሱልጣኔት (13ኛው ክፍለ ዘመን) ጊዜ ጀምሮ በክርስቲያን ደጋማውያን እና በምስራቅ በመጡ ሙስሊሞች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ውስጥ ነበር።  አብዛኛው ቀደምት ግጭት የተካሄደው በደቡብ በኩል በምስራቅ ድንበር ነበር። አሁን ሸዋ ነው።   ነገር ግን በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንጎት አሁን ራያ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በአዳል ጀነራል አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ጋዚ ጦር እና በኢትዮጵያው አጼ ልብነ ድንግል ከፍተኛ ግጭት ጊዜ የውጊያ መዐከል ነበር። ይህ አስነዋሪ የግጭት ዘመን የኢትዮጵያና የአዳል ጦርነት በመባል ይታወቅ ነበር።  አጼ ልብነ ድንግል የካቲት 10 ቀን 1541 ምጽዋ ወደብ ከደረሱት ፖርቹጋሎች እርዳታ ጠየቁ። በሚያዚያ ወር 1542 የሁለቱ ሠራዊት ከአሸንጌ  ሃይቅ በስተሰሜን በኮረም አካባቢ ተገናኙ። ይህም ውጊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ ጦር መ...

የወላይታ ንጉስ ካኦ ጦና

በዳዊት ፀሐይ  ካኦ ጦና በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ የገዛ የወላይታ ንጉስ ነበር።  ወላይታ በደቡብ ኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የሚገኝ ክልል ነው።  የራሱ የሆነ ቋንቋ እና ባህል ያለው የወላይታ ህዝብ መኖሪያ ነው።  ክልሉ በቡና ምርት የሚታወቅ ሲሆን በተፈጥሮ ውበቱ የቱሪስት መዳረሻም ነው።  እናም ካኦ ጦና በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን የኢትዮጵያን ግዛት መስፋፋት በመቃወም ይታወቃሉ።  ካኦ ቶና ህዝቡን እየመራ ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ተከታታይ ጦርነት ቢያደርግም በመጨረሻ ግን ተሸንፎ እጅ ለመስጠት ተገደደ።  በስደት ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ኖረ።  ካኦ ቶና ቢሸነፍም በወላይታ ህዝብ ዘንድ እንደ ጀግና ሲታወስ ቆይቷል።  ትሩፋቱ በወላይታ አፈ ታሪክ እና ዘፈኖች የተከበረ ሲሆን ታሪኩ አሁንም ጭቆናን እና ኢፍትሃዊነትን ለመቃወም ይውላል። ስለ ጦርነቱ ማለትም ስለ ካኦ ጦና እና ዳግማዊ አጼ ምኒልክ መካከል ስለተደረጉ ጦርነቶች ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይቻላል።  ሆኖም ካኦ ጦና ህዝባቸውን በመምራት በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ተከታታይ የሽምቅ አይነት ጥቃቶችን ማለትም እንደ ማሸማቀቅ እና መምታት የመሳሰሉ ስልቶችን ሲጠቀሙ እንደነበር ታሪክ ያወሳል። ዳግማዊ አፄ ምኒልክም አመፁን ለመደምሰስ ብዙ ጦር ልከው ነበር።  ጦርነቱ ለብዙ አመታት የዘለቀ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባቸዋል።  በመጨረሻም ካኦ ጦና ተሸንፎ እጅ ለመስጠት ተገዷል።  በስደት ወደ አዲስ አበባ ተወስዶም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ኖሯል። ፊታውራሪ ደስታ ፍስሐ የካኦ ጦና ልጅ