ይህ ፎቶ የተነሳው በደማስቆ በ1899 ነው። ድንክዬው ሰሚር ነው ክርስቲያን ነው። መራመድ አይችልም።. በጀርባው የተሸከመው ደግሞ መሐመድ ነው። ሙስሊም ነው ማየትም የተሳነው ነው።
መሐመድ መንገድ መሪ አይፈልግም በሰሚር ይተማመናል። ሳሚር ደግሞ የጓደኛውን ጀርባ ተጠቅሞ የከተማዋን ጎዳናዎች ይቃኛል። ሁለቱም ወላጅ አልባ ልጆች ነበሩ እና በአንድ ክፍል ውስጥ ይኖሩ ነበር.
ሰሚር የመተረክ ስጦታ ነበረው እና " አንድ ሺ ቀን እንደ አንድ ቀን ለሊት! " የሚለውን ተረት በደማስቆ ለሚገኝ ካፌ ደንበኞች ይተርክ ነበር። መሀመድ እዚያው ካፌ ፊት ለፊት ቦልቦላዎችን እየሸጠ የጓደኛውን ታሪክ ማዳመጥ ይወድ ነበር።
አንድ ቀን ወደ ክፍሉ ሲወጣ መሐመድ ጓደኛውን ሞቶ አገኘው። ለጓደኛው ለሰባት ቀናት ያህል አለቀሰ። ከሰባት ቀንም በውኃሏ ጓደኛውን ተከትሎ እሱም አረፈ። የተለያየ ሃይማኖት ተከታይ በመሆናቸው እንዴት በጥሩ ሁኔታ እንደተግባቡ ሲጠየቁ
በእጁ ወደ ልቡ እያመለከተ "እነሆ እኛ አንድ ነበርን" አለ።

Comments
Post a Comment