በከተሞችና አጎራባች ቀበሌዎች ሽብር ለመፍጠር ታስቦ የነበረ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ።
***
ከጉባይ ገንዳውኃ ከገንዳውኃ ጭልጋ ለማንቀሳቀስ ታስቦ የነበረ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በወረዳው የጸጥታ ኃይል በቁጥጥር ስር ዋለ።
በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ በጉባይ ቀበሌ ጥቅምት 02/2015 ዓ.ም ከምሸቱ 1:00 ሰዓት ላይ ጓዴ አውለውና ታምራት የተባሉ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በከተሞችና በተለያዩ አካባቢዎች ሽብር ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ በተደረገው ጥምር የጸጥታ ሀይል ኦፕሬሽን ሊሄድ ከነበረ 40 f1 ቦንብ እስከ ፊውዙ ድረስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰጠኝ አሰፋ ገልጿል፡፡
በተሰራው ኦፕሬሺን ጓዴ አውለው እና ታምራት አየልኝ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከተያዙት ፀረ-ሰላም ኃይሎች አንዱ ጓዴ አውለው ቋም ክላሺ እስከ 30 ጥይት ድረስ እጂ ከፈንጂ መያዙን ነው የገለፁት አቶ ሰጠኝ፡፡
ይህ ኦፕሬሺን በዞን ከፍተኛ አመራሮች እና በወረዳ የፀጥታ ሃይል በተሰጠ ስምሪት የተገኘ ውጤት መሆኑን ነው አቶ ሰጠኝ የገለፁት፡፡
ይህንና መሰል ህገ-ወጥነት ከማህበረሰባችን ጋር በመሆን መከላከል ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የመተማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን
ጥቅምት 4/2015 ዓ.ም


Comments
Post a Comment