የበላይ ዘለቀ፣ የዳግማዊ ቴዎድሮስ...ልጆች!
አናብስቱ እንደአራስ ነብር ይወራጫሉ፤ ጀግንነት ከአባቶቻቸው የወረሱት ክብራቸው፤ ምሽግን መደርመስ፣ አቀበት መውጣት፣ ቁልቁለት መውረድ፣ አልሞ አለመሳት ያደጉበት የጀግንነት ማማ። ትዕግስታቸው ጫፍ ድረስ መሆኑ የማይደራደሩበት ኢትዮጵያዊ ስነልቦና ከፍታቸው ማሳያ ሰገነት ነው።
በሁሉም አቅጣጫ የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት ተወጥተዋል። አሁን ፈንታው ደጀን ሆነው አካባቢያቸውን በጥንቃቄ መቃኘትና የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን መከላከል ብቻ። ድሉን ከወዲሁ አጣጥመው ታሪክ የማይረሳው ጀብድ ፅፈዋል። ፈጣሪ ቢፈቅድና ብንኖር ገድላቸውን በጦማር ሰንደን፤ በክብር ደጉሰን ለትውልድ እናስተላልፋለን።
-
ታየ ቦጋለ አረጋ (ኢልመ ደሱ ኦዳ)
ዘነጌሌ ቦረና ቦረናወጉጂ
ፀረ-ጎጠኛ የታሪክና የሀገር ፍቅር ሚኒስትር

Comments
Post a Comment