Skip to main content

ሁለት ዓመት የደፈነው ጦርነት ሲታወስ

 


ከአሁን በኋላ ህወሃትን የቆላ ተንቤን ተራሮች ያድኑት ይሆን?!

የትግራይ ዕጣ ፋንታስ? በህወሃት መሸነፍ በኢትዮጵያ  ሰላምን ያመጣ ይሆን?!

ህወሃት ቀለበት ውስጥ ገብቷል። የህወሃት የመጨረሻዋ ምሽግ መቀሌም በጥምር ጦሩ እጅ መግባቷ ቅርብ ይመስላል። እንዲህ ከሆነ  ህወሃት መጨረሻ ሊሆን ይችላል?! የጦርነቱ  አጀማመር እና ፍፃሜስ?!  

...............///..............

ይህ ልዩ ትንታኔ ነው።

ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም

................///..............

ሁለት ዓመት የደፈነው የህወሃት ጦርነት  ለሁለተኛ ጊዜ  ሊቋጭ ዳር የደረሰ ይመስላል። ጦርነቱ የፈነዳው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም መሆኑ ይታወሳል። የጦርነቱ መፈንዳት መንስኤ ህወሃት ሰሜን እዝን አጥቅቶ መሳሪያ በመዝረፉ ነው። በወቅቱ ህወሃት እስከ 500 ኪሎሜትር የሚወነጨፍ ሪሲያ ሰራሽ ሚሳኤል ነበረው። እነዚህ ሚሳኤሎች ወደ ባህርዳር እና አስመራ ለተከታታይ ተወንጭፈዋል።  የህወሃቱ አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ አራት ኪሎን ጨምሮ በሚሳኤል እንመታለን በወቅቱ ብሎ ነበር።

ህወሃት ጦርነቱን ሲጀምር የራሱን ደጋፊ የመከላከያ ሀይል በማስከዳት ነበር።  ይህ ሆኖ ግን  ህወሃት በወቅቱ የነበረኝ 9 ሺ ልዮ ሀይል ብቻ ነው ብሎ ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ ሰራዊት ቁጥር ወደ 170 ሺ ይደርስ ነበር። ከዚህ ውስጥ ወደ 50 ሺው የህወሃት ነበር። በተለይም አዛዦች፣ የመስመር መኮንኖች፣ ጀኔራሎች፣ ፈንጅ ቀማሚዎች እና አምካኞች፣ መድፍ እና ታንክ ተኳሾች በብዛት ከህወሃት የነበሩ መከላከያዎች ነበሩ።

እነዚህ ሁሉ ከመከላከያ ጠርጎ ህወሃት ጦርነቱን ጀመረ። ነገርግን ህወሃት በዚህ ወቅት መከላከል የቻለው ለሁለት ሳምንት ብቻ ነበር።  ህዳር 19 ቀን 2013 ዓም መቀሌ ተያዘች። ህወሃት ቀደም ብሎ ህዳር 14 ቆላ ተንቤን በረሃዎች ውስጥ መሽጓል። ህወሃት ወደ አራት ኪሎ ለመሻገር አስቦ የቀሰቀሰው ጦርነት ፣ አራት ኪሎ መግባቱ ቀርቶ ቆላ ተንቤን በረሃ አስገባው። በዚህ ወቅት የህወሃት  መሸነፍ ዋነኛ መንስኤው  የኢትዮጵያ ሰራዊት ከኤርትራ፣ ከአፋር እና ከአማራ ልዮ ሀይል ጋር መጣመሩ ነበር። ከዚህም ባለፈ ህዘሃት ያልጠበቀው ድሮን ነበር። ከቀይ ባህር ዳርቻዎች የሚነሱ የአረብ ኤሜሬት ድሮኖች የህወሃትን ሚሳኤል፣ ታንክ፣ መድፍ ዶግ አመድ አደረጉት። ህወሃት እንዲህ አልገመተም። ህወሃት አተረፍ ባይ አጉዳይ ሆኖ ከህዳር 19 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓም ለስምንት ወር ያህል መቀሌ ለቆ ጫካ ተቀመጠ።

በዚህ ስምንት ወር ውስጥ ብልፅግና መሩ መንግስት በድል አድራጊነት አሸሸ ገዳሜ ሲል ባጀ። በወሌቃይት በኩልም የሰሊጥ ስርቆው ተፋፋመ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም በፓርላማ ህወሃት ተኗል፣ ዱቄት ሆኗል፣ ህወሃት የሚባል የለም። ካሁን በሗላ ህወሃት ታጥቆ ሊወጋን አይችልም አሉ። ህዝቡም ይሄን አመነ። ተከፋይ አክቲቪስቶችም በሰበር ዜና ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተደምሶ የአካል ክፍሉ ተለያይቶ እግሩ መድሃኒዓለም፣ ጭንቅላቱ ጊዮርጊስ ተቀበረ እያሉ አቧለቱ።  በዚህ ሁኔታ ጌታቸው ረዳ እና ጀኔራል ፃድቃን ጨምሮ ሁሉም በሰበር ዜና ቢያንስ ለአስር ጊዜ ተደመሰሱ፣ ተከበቡ፣ ተገደሉ ተባለ።

የብልፅግና አገዛዝም ከብልፅግና በተቃራኒ ሀሳብ የሚሰጢትን ሁሉ ህወሃትም ተሸንፏል ፣ ጃዋርም ታስሯል፣ ካሁን በሗላ ብልፅግናን መቃወም በከንቱ መድከም ነው እያሉ ሰኔ 14 ቀን 2013 ለተደረገው ምርጫ ቀሰቀሱ። ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓም በተደረገ ምርጫ ከጎጃም በስተቀር ብልፅግና በሁሉም አካባቢዎች አሸነፈ። ጎጃም ብቻ በተወሰነ ወረዳዎች ባህርዳርን ጨምሮ አብን አሸነፈ። በዚህ ምክንያት ከጎጃም በፌዴራል ደረጃ አምስት የህዝብ ተዘካይ አባላት፣ በክልል ደግሞ ወደ 13 ተወካዮች ከአብን ተመረጡ።

በምርጫ እና በወንበር ልፊያ ላይ ሆኖ አገዛዙ ህወሃት ተዘንግቶ ነበር። ነገርግን ከግንቦት 9 ቀን እስከ ሰኔ 21 ህወሃት ዘመቻ አሉአባነጋ  ብሎ የሀገር መከላከያ ሰራዊት   ጥቃት ከፈተበት።መስመራዊ  መኮንኖች ተገደሉ። ትግራይ ውስጥ የገባው መሳሪያ ሙሉ በሙሉ  ሳይወጣ ቀረ። ህወሃት መቀሌን ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓም ዳግም ተቆጣጠረ። በብልፅግና ተቋቁሞ የነበረው የትግራይ ጊዚአዊ አስተዳድር  ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ኮበለለ።

ህወሃት ትግራይን ከተቆጣጠረ በሗላ በቀጥታ ሀምሌ አንድ 2013 ዓም ጀምሮ ወደ አማራ እና አፋር ወረራ ጀመረ።

በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ የነበራት የሰራዊት ቁጥር 12 ክፍለጦር  ሲሆን በቁጥር ሲገለፅም ወደ 44 ሺ ብቻ ነበር። ህወሃት ደግሞ  የብልፅግና መንግስት ሲንጫጫ ወደ 300 ሺ ታጣቂ በመቶ ክፍለጦር ጫካ ሆኖ አደራጅቷል። እናም ህዝባዊ ማዕበል በመፍጠር በሰሜን ጎንደር በኩል ከጎንደር በቅርብ ርቀት ቆላ ወገራ ድረስ እስከ ነሀሴ 2013 ዓም ሲስፋፋ፣ አሁንም ነሀሴ ላይ በደቡብ ጎንደር በኩል እስከ ደብረታቦር ደረሰ። ህዳር 2014 ህወሃት በቀጥታ ወደ አዲስአበባ እየገሰገሰ ከአዲስአበባ 200 ኪሎሜትር ርቆ ደብረሲና ደረሰ።

ደብረሲና ከደረሰ በሗላ አዳዲስ ምልምሎች ሰልጥነው ወደ ጦርነቱ ገቡ። አማራ ክተት ተባለ። ፋኖ ተሰማራ። ሰማዮ የድሮን መንገድ ሆነ። ህወሃት ከመቀሌ ርቆ ስለመጣ ወገቡን መሃል ላይ ሲመታ ጎበጠ። እናም ህወሃት ከደብረሲና ወደ ቆቦ እግሩን ሰበበ።ታህሳስ 2014 ህወሃት ከደብረሲና ተነስቶ የሗሊት ሩጦ ቆቦ ደረሰ።

ነገርግን ህወሃት ከሰሜን ጎንደር  አዳርቃይ እና ጠለምትን፣ ከዋግኸምራ አበርገሌ እና ፃግብጅን፣ ከሰሜን ወሎ የራያ የተወሰኑ ቀበሌዎችን ጨምሮ ኮረም አላማጣን  ተቆጣጥሮ ከረመ። ወደ አንድ ሚሊየን አማራ በህወሃት ስር ሆኖ ለዓመት ተሰቃይቷል።

ህወሃት ነሀሴ 18 ቀን 2014 ዓም ዳግሞ ጦርነት ቀሰቀሰ ና ዋጃ አካባቢን ጨምሮ እስከ ወልዲያ ጫፍ ተቆጣጠረ። ይህ የህወሃት ሶስተኛ ጥቃቱ ነው።  የኤርትራ ጦር ከጀግናው የሀገር መከላከያ፣ ልዮ ሀይል እና ሚኒሻ፣ ፋኖ ተጣምሮ በህወሃት ላይ የመከላከል እርምጃ ወሰደ።

ህወሃት ከወር በሗላ አዳርቃይን፣ ማይጠብሪን፣ ሽሬን፣ ቆቦን፣ አላማጣን፣ ኮረምን  ለቀቀ። በሰሜን በኩል ሽራሮን፣ ዛላአንበሳን፣ ራማን፣ ፆረናን፣ አዲግራትን  ለቀቀ።

የኢትዮጵያ መንግስትም ወደ መቀሌ እገባለሁ። የሽሬ፣ የአክሱም፣ የመቀሌ አየር መንገዶችን እቆጣጠራለሁ አለ። አሁን ህወሃት  ለሶስተኛ ጊዜ ወሮ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ተሸንፏል። መቀሌ ከተያዘች የህወሃት አመራሮች እጅ መስጠት ወይም መደምሰስ ብቸኛ እጣቸው ይሆናል። ምክንያቱም መደበቂያ ዋሻቸው በሙሉ እየተዘጋ ነው። ነፃ በወጡ አካባቢዎች መንግስታዊ አስተዳድር እየተዘረጋ፣ ትራንስፓርትም በጎንደርም በወሎም በኩል ክፍት ሆኗል። ነፃ የወጣው አካባቢ ሰባዊ እርዳታ ይደርሰዋል። ቁጥጥሩ ከባድ ስለሆነ ቄስ መስሎ በቤተክርስቲያን፣ ሸህ መስሎ በመስጊድ፣ ገበሬ መስሎ በማሳ፣ እንደ ሽፍታ በጫካ ተደብቆ ማምለጥ የሚቻል አይመስልም። ጦርነቱ በዚህ ከቀጠለ እነ ደብረፅዮን፣ እነ ጀኔራል ታደሰ  መማረክ ወይም መደምሰስ የዕጣ ክፍላቸው ሊሆን ይችላል።

ሳተናው ከዲፕሎማሲ ምንጮች እንደሰማው ግን የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ህወሃትን ለማዳን መንቀሳቀሳቸው አይቀርም እየተባለ ነው። የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ከገፋ  የአውሮፓ ህብረት የወንድ በር ለህወሃት ባለስልጣናት ይሰጣል እየተባለ ነው። ጁቡቲ ላይ ያለው የአሜሪካ እና የፈረንሳይ ጦር እነ ጀኔራል ፃድቃንን መቀሌ ከመከበቧ በፊት በጦር ጀት ሊያስወጧቸው ይችላሉ እየተባለ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ  ተደራደሩ በሚል እነ አሜሪካ ለህወሃት እድሜ ሊቀጥሉ ይችላሉ።  እነ አሜሪካ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከባድ ቅጣት ለመጣል ውይይት ላይ መሆናቸው ይታወቃል።  ስለዚህ የህወሃት ብቸኛ ተስፋ አውሮፓ እና አሜሪካ ናቸው። ካለበለዚያ ህወሃትን ካሁን በሗላ የሚያድነው ጫካ የሚኖር አይመስልም።

ህወሃት ከተሸነፈ  የትግራይ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያ ጋር በአብሮነት ይኖራል፣ ሱዳንም ከኢትዮጵያ እጇን ትሰበስባለች። ኤርትራም ሱዳንን ልትመታት ትችላለች። ኤርትራ ገናና ትሆናለች። ሩሲያም ቀይ ባህር ላይ የጦር ሰፈር ልትመሰርት ትችላለች።ፐምስራቅ አፍሪካን ሩሲያ እና ቻይና ገናና ሊሆኑበት ይችላሉ። አሜሪካ እና አውሮፓ  ከምስራቅ አፍሪካ ሊገፉ ይችላሉ። ለዚህም ይመስላል አሁን አውሮፓውያን ህወሃትን ለማዳን የሞት ሽረት ትግል ውስጥ የገቡት።

ህወሃት ከተሸነፈ በኢትዮጵያስ ምን ይመጣል ለሚለው መመለስ አለበት። የብልፅግና መንግስት አውራ ይሆናል። ተፎካካሪ ፓርቲዎች ይሟሽሻሉ። ኦነግ ተስፋ ቢያጣም ጥቃቱን ይቀጥላል።    ብልፅግና መሩ መንግስት መሰረታዊ ማሻሻያ ካላደረገ በስተቀር በኢትዮጽያ ሰላም ላይመጣ ይችላል። አውሮፓውያን  በተመድ በኩል የጦር ወንጀል ተፈፅሟል ብለው በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ክስ ሊመሰርቱ ይችላሉ።

በመሆኑም የህወሃት መሸነፍ ብቻ  ብቸኛ የሰላም ምንጭ አይሆንም። ዋናው ነገር ሀቀኝነትን፣ ፍትህን፣ እውነተኛ አስተዳድርን መዘርጋት ለሰላም መስፈን አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብሎ ሳተናው ያምናል።

………………..


Comments

Popular posts from this blog

አርሲ እና የአርሲ ሴቶች ባህል

  በዳዊት ፀሐይ አርሲ በማዕከላዊ የኢትዮጵያ ክፍል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኝ ክልል ነው።  በዋናነት በአካባቢው በሚኖሩ በአርሲ ሰዎች ስም ተሰይሟል።  የአርሲ ዞን ወደ 17,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ከ3 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይኖራል።  ክልሉ በተለያዩ መልክዓ ምድሮች የሚታወቅ ሲሆን ይህም ደጋ፣ ቆላማ እና ደኖችን ያጠቃልላል።  በተጨማሪም የላንጋኖ ሀይቅ እና የዝዋይ ሀይቅን ጨምሮ የበርካታ ወንዞች እና ሀይቆች መኖሪያ ነው።  በአርሲ ያሉ አብዛኛው ሕዝብ ዋናው የገቢ ምንጭ ግብርና ነው።  ክልሉ ቡና፣ ሻይ፣ በቆሎ፣ ስንዴ እና ሌሎች ሰብሎችን በማምረት ይታወቃል።  የእንስሳት እርባታ የኢኮኖሚው አስፈላጊው አካል ነው። አርሲ ካሏት ባህላዊ ቅርሶቿ በተጨማሪ የበርካታ ታሪካዊ ቦታዎች ባለቤትም ናት።  ከእነዚህም መካከል በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጀመረው አዳዲ ማርያም ውቅር ቤተ ክርስቲያን እና የሶፍ ኦማር ዋሻ ( ከአፍሪካ ትልቁ የዋሻ ስርዓት አንዱ ነው። ) ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው፠ በአጠቃላይ አርሲ ልዩ የሆነ ባህልና ታሪክ ያላት በመልክአ ምድርና በተፈጥሮ ሀብት በእጅጉ የበለጸገች  ክልል ናት። በአርሲ ባህል ሴቶች ትልቅ ሚና አላቸው።  ቤተሰብን የማስተዳደር፣ ልጆችን የማሳደግ እና በቤተሰቡ ገቢ ላይ በእርሻ ወይም በትንንሽ ንግዶች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው።  ሴቶች በማህበረሰብ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች በተለይም ከማህበራዊ ደህንነት እና ልማት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ። በአለባበስ ረገድ የአርሲ ሴቶች በተለምዶ ሸማ የሚባል የባህል ልብስ ይለብሳሉ። ከጥጥ የተሰራ እና በቀለማት ያሸበረቀ ነው።...

ነጻ የወጣችውን ራያ ቆቦን ወገን ለመቼ ነው በሚል ስፍራው ጋ ደርሰን የህዝቡን አኗኗር እና ስነ ልቦና አይተናል።

   ከብዙ በጥቂቱ ፥ ከሙሉ በክፍሉ ነጻ የወጣችውን ራያ ቆቦን ወገን ለመቼ ነው በሚል ስፍራው ጋ ደርሰን የህዝቡን አኗኗር እና ስነ ልቦና አይተናል።ከሁለት ዓመት በውኋላ ተቋርጦ የነበረው መብራት ስለ መጣ ከተማው በተኩስ ሲናጥ አድሯል።   ቆቦ በሰሜን ኢትዮጵያ ÷ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የምትገኝ ከተማ ናት  ቆቦ ከባህር ጠለል በላይ 1468 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች።   ቆቦ በምዕራብ በኩል በኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች እና በምስራቅ በአፋር የእሳተ ጎሞራ ጭንቀት ያዋስናታል።  በታሪክ ራያ አንጎት ተብላ ትጠራ ነበር። ራያ ቆቦ የአማራ ህዝብ ነው። አንጎት በአማራ ክልል ወልድያ አቅራቢያ ከሀብሩ ወረዳ በደቡብ በኩል እስከ ማይጨው ራያ አዘቦ የሚደርስ ሜዳ ነው።  ይህ ስፍራ ከኢፋት ሱልጣኔት (13ኛው ክፍለ ዘመን) ጊዜ ጀምሮ በክርስቲያን ደጋማውያን እና በምስራቅ በመጡ ሙስሊሞች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ውስጥ ነበር።  አብዛኛው ቀደምት ግጭት የተካሄደው በደቡብ በኩል በምስራቅ ድንበር ነበር። አሁን ሸዋ ነው።   ነገር ግን በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንጎት አሁን ራያ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በአዳል ጀነራል አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ጋዚ ጦር እና በኢትዮጵያው አጼ ልብነ ድንግል ከፍተኛ ግጭት ጊዜ የውጊያ መዐከል ነበር። ይህ አስነዋሪ የግጭት ዘመን የኢትዮጵያና የአዳል ጦርነት በመባል ይታወቅ ነበር።  አጼ ልብነ ድንግል የካቲት 10 ቀን 1541 ምጽዋ ወደብ ከደረሱት ፖርቹጋሎች እርዳታ ጠየቁ። በሚያዚያ ወር 1542 የሁለቱ ሠራዊት ከአሸንጌ  ሃይቅ በስተሰሜን በኮረም አካባቢ ተገናኙ። ይህም ውጊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ ጦር መ...

የወላይታ ንጉስ ካኦ ጦና

በዳዊት ፀሐይ  ካኦ ጦና በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ የገዛ የወላይታ ንጉስ ነበር።  ወላይታ በደቡብ ኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የሚገኝ ክልል ነው።  የራሱ የሆነ ቋንቋ እና ባህል ያለው የወላይታ ህዝብ መኖሪያ ነው።  ክልሉ በቡና ምርት የሚታወቅ ሲሆን በተፈጥሮ ውበቱ የቱሪስት መዳረሻም ነው።  እናም ካኦ ጦና በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን የኢትዮጵያን ግዛት መስፋፋት በመቃወም ይታወቃሉ።  ካኦ ቶና ህዝቡን እየመራ ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ተከታታይ ጦርነት ቢያደርግም በመጨረሻ ግን ተሸንፎ እጅ ለመስጠት ተገደደ።  በስደት ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ኖረ።  ካኦ ቶና ቢሸነፍም በወላይታ ህዝብ ዘንድ እንደ ጀግና ሲታወስ ቆይቷል።  ትሩፋቱ በወላይታ አፈ ታሪክ እና ዘፈኖች የተከበረ ሲሆን ታሪኩ አሁንም ጭቆናን እና ኢፍትሃዊነትን ለመቃወም ይውላል። ስለ ጦርነቱ ማለትም ስለ ካኦ ጦና እና ዳግማዊ አጼ ምኒልክ መካከል ስለተደረጉ ጦርነቶች ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይቻላል።  ሆኖም ካኦ ጦና ህዝባቸውን በመምራት በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ተከታታይ የሽምቅ አይነት ጥቃቶችን ማለትም እንደ ማሸማቀቅ እና መምታት የመሳሰሉ ስልቶችን ሲጠቀሙ እንደነበር ታሪክ ያወሳል። ዳግማዊ አፄ ምኒልክም አመፁን ለመደምሰስ ብዙ ጦር ልከው ነበር።  ጦርነቱ ለብዙ አመታት የዘለቀ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባቸዋል።  በመጨረሻም ካኦ ጦና ተሸንፎ እጅ ለመስጠት ተገዷል።  በስደት ወደ አዲስ አበባ ተወስዶም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ኖሯል። ፊታውራሪ ደስታ ፍስሐ የካኦ ጦና ልጅ