የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ!!
የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ባጣናቸው የህዝብ ልጅ ማዲንጎ አፈወርቅ፣ለምስራቅ አማራ ፋኖ አባል አሸናፊ አለሙ እና በወለጋ በሞቱት ንፁሃን እናቶች፣አባቶች፣እህቶች ወንድሞች ህፃናት የደረሰብንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን የሚፈሱት እያንዳንዱ የደም ጠብታ የሚወርዱት የመከራ ናዳ ህዝባችንን ትንሳኤ ለማምጣት የሚያፋጥኑ ናቸው።
በብዙ መከራ ውስጥ ብንሆንም የአማራ ህዝብ የሚድንበትን እና ይህን የመከራ ችግር የሚያልፍበትን መንገድ ይቀይሳል። ማህበራችንም በነዚህ እና መሰል ችግሮች ውስጥ ሆኖ ለመላው የአማራ ህዝብ እና ለማህበራችን ደጋፊዎች አባላት ማህበሩ መስከረም 2015ዓ.ም አንደኛ መደበኛ ጉባኤ አድርጓል።በዚህም ማህበሩ ያሉበትን ክፍተቶች አሟልቶ ስብሰባውን አድርጓል።
በዚህም ጉባኤ ማህበሩ ኮሚቴውን በማጠናከር ስብሰባውን ጀምሯል። ስብሰባውን ሲጀምር ከታች ያሉትን ኮሚቴዎች ሹመት በማፅደቅ ጀምሯል፦
• ሰብሳቢ
• ፀሃፊ
• ህዝብ ግንኙነት
• ጥናት አና እስትራቴጂ
• አካውንታት
• ሂሳብ ሹም
• ግዥና ሃብት አሰባሳቢ
• ክልላዊና ሃገራዊ የህዝብ ትስስር
• ባህልና ቅርስ ኦፊሰር
• ቅሬታ ሰሚ ኦፊሰር
• ሚዲያና ኮሚኒኬሽን
• አዛውንቶች ሴቶች
• ኪነጥበብ ስራወች
• ኪነጥበብ ስራወች
• ታሪክና ጥናት ሃላፊ
• አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ
• የህግ አማካሪ
በቀጣይ የሚሰራቸውን ስራዎች በእቅድ አስቀምጦ።በክልላችን ያሉትን ችግሮች በመልቀም ከክልላችን ውጪ ያሉትንም የህዝቦቻችንን ስቃይ በጠነከረ የህዝብ ትግል በጋራ ያመጣነውን የትህነግ ለውጥ አሁን በለቅሶ ሳይሆን በጠንካራ የህዝብ ትግል አዲስ ለውጥ ለማምጣት በጋራ ቃል ገብቶ ስብሰባውን አጠናቋል። ህዝባችንም እየታዩ ያሉት አማራን የማጥፋት ስራ ለማክሸፍ እራሱን እንዲያዘጋጅ ጥሪ አቅርቧል።
በመጨረሻም የአማራ የፀጥታ ሀይል ማለትም ፖሊስ፣ልዩሀይል አርማ ብተና በተረኝነት በትር እየቆሰለ ካለው የህዝብ ልጅ ጎን ሆኖ ከፋኖ ወንድሞቹ ጋር በጋራ በመቆም እራሱን እንዲጠብቅ ለእውነት ዘብ እንዲሆን በማለት ጉባኤውን ቋጭቷል።

Comments
Post a Comment